BBC News, አማርኛ - ዜና
BBC News Amharic Top Stories
በደቡብ ወሎ መውጫ ያጡ የማዕድን ቆፋሪዎች ቤተሰቦች ከ19 ቀናት በኋላ ሐዘን ተቀመጡ
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ከ19 ቀናት በፊት የማዕድን ማውጫ ዋሻ የተናደባቸውን ሰዎችን ለማውጣት ሲጥሩ የነበሩት ቤተሰቦች እና የአካባቢ ነዋሪዎች፤ ማዕድን አውጪዎቹን በሕይወት የማግኘት ተስፋቸው ተመናምኗል።
በአንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች “ከባድ ውጊያ” ማገርሸቱን ነዋሪዎች ተናገሩ
ካለፈው ሳምንት መገባደጃ አንስቶ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ማገርሸቱን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ከደብረ ብርሃን ወደ ደሴ የሚወስደው መንገድ ከቅዳሜ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ መዝጋቱ ይታወሳል። መከላከያ በደቡብ ሜጫ አካባቢ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጹ ላይ ገልጿል። ኮማንድ ፖስቱ እና መከላከያ “ፅንፈኛ” ባሏቸው ኃይሎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
ሚስቱን እና ሦስት ልጆቹን ጨምሮ 103 ዘመዶቹን ያጣው ፍልስጤማዊ አባት
እስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄደችው ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ምክንያት የአሕመድ አል-ጉፈሪ ቤተሰቦች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አልቀዋል። በጋዛ ከተማ በቤተሰቦቹ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 103 ዘመዶቹ ተገድለዋል። እሱ የተረፈው 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በዌስት ባንኳ ኢያሪኮ ከተማ ስለነበረ ነው።
ደም ግፊትን ዝቅ ማድረግን ጨምሮ ቀይ ሥር የሚሰጣቸው አምስት ጥቅሞች
የቀይ ሥርን ለየት ያለ ጠቅምን በተመለከተ የሥነ ምግብ እና የጤና ባለሙያዎች መረጃዎችን እያጋሩ ሲሆን፣ በዕለት ከዕለት ምግባችን ውስጥም ቀይ ሥርን እንድናካትት እየመከሩ ነው። ቀይ ሥር የደም ግፊትን እንዴት ሊቀንስ ይችላል? እንዴትስ ነው መመገብ ያለብን?
ለ68 ሕጻናት ሞት ምክንያት ከሆነ ሽሮፕ ጋር በተያያዘ 23 ሰዎች ተፈረደባቸው
ለ68 ህጻናት ሞት ምክንያት ነው ከተባለው የተመረዘ የሳል ሽሮፕ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 23 ሰዎች ኡዝቤክስታን ውስጥ ተፈረደባቸው።
በቡርኪና ፋሶ ታጣቂዎች መስጂድ እና ቤተ ክርስቲያን ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካቶችን ገደሉ
ቡርኪና ፋሶ ውስጥ በአንድ መስጂድ እና ቤተክርስቲያን ላይ በተመሳሳይ ቀን በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።
የአንድ ቢሊየን ዶላር ልገሳ ያገኛው የአሜሪካው ዩኒቨርስቲ ዶክተሮችን በነጻ ሊያስተምር ነው
የአሜሪካው ኒው ዮርክ ዩኒቨርስቲ የህክምና ትምህርት ቤት አንድ ቢሊየን ዶላር ልገሳ ከአንዲት ግለሰብ በማግኘቱ የህምክና ትምህርት ከክፍያ ነጻ ሊሰጥ ነው።
“ከሰው በታች አድርገው ነው የሚቆጥሩን”- ‘የሦስተኛ አገር ዜጋ’ የተባሉት ከዩክሬን የሸሹ አፍሪካውያን ተማሪዎች
የዩክሬን ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በአገሪቱ በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ሲማሩ የነበሩ አፍሪካውያን ከዩክሬን ለቀው ወጥተው ነበር። የተወሰኑት በሌሎች የአውሮፓ አገራት ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን፣ ሌሎቹ ግን የለፉበትን ትምህርታቸውን ለማጠናቀቅ ወደ ዩክሬን ተመልሰዋል። ሁሉም በያሉበት ችግር ላይ እንደሆኑ ይናገራሉ።
ፈረንሳዊው የ“አፍሪካ ኢንተለጀንስ” ጋዜጠኛ እና የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ታሰሩ
የ“አፍሪካ ኢንተለጀንስ” ድረ ገጽ ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ “ከፋኖ እና ኦነግ ሸኔ ጋር በመተባባር ሁከት እና ብጥብጥ ለማስነሳት በመንቀሳቀስ” ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በአማራ ክልል ከሕግ ውጪ ግድያ እንዲቆም እና ፈጻሚዎች ለሕግ እንዲቀርቡ አምነስቲ ጠየቀ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአማራ ክልል እየተካሄደ ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ከሕግ ውጪ ይፈጽማል ያለውን ግድያ እንዲያቆም እና በድርጊቱ የተሳተፉ ተጠያቂ እንዲሆኑ ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።
በዋሽንግተን የእስራኤል ኤምባሲ ደጃፍ እራሱን በእሳት ያቃጠለው የአሜሪካ የአየር ኃይል አባል ሕይወቱ አለፈ
ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ከሚገኘው የአስራኤል ኤምባሲ ፊት ለፊት እራሱን በእሳት ያቃጠለው የአሜሪካ የአየር ኃይል አባል በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ሕይወቱ አለፈ።
የብራዚል የቀድሞ ፕሬዚዳንት የቀረበባቸውን የመፈንቅለ መንግሥት የሙከራ ክስ አስተባበሉ
የብራዚል የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጄይር ቦልሶናሮ ስልጣናቸውን ከለቀቁበት አንድ ዓመት ጀምሮ በርካታ ፖለቲካዊ ጥቃቶችን እያስተናገዱ እንደሆነ ተናገሩ።
አነጋጋሪ ጉዳይ
የ1966ቱን የሙስሊሞች ሰልፍ በኅቡዕ ያስተባበሩት እነማን ናቸው?
በኢትዮጵያ አብዮት ተካሂዶ ንጉሣዊው ሥርዓት ካበቃ እነሆ 50 ዓመት ሆነው። ለሥር ነቀሉ አብዮት መከሰት ምክንያት ከሆኑት መካከል የፊውዳሉ ሥርዓት የቆመበት የመሬት ሥሪት እና የብሔር ጥያቄ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን፣ የእምነት እኩልነት ጥያቄም ውስጥ ውስጡን ሲብላላ ነበር። በተለይ አብዮቱ ዋዜማ በአዲስ አበባ የተካሄደው የሙስሊሞች ሰልፍ ጉዳዩን አደባባይ ያወጣ ክስተት ነበር። ያ ግዙፍ ሰልፍ እንዴት እና በማን ተደራጀ?
በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎቿ ስህተት የኢትዮጵያ እና የኳታር አውሮፕላኖች ሊጋጩ ነበር መባሉን ሶማሊያ አስተባበለች
በሶማሊያ የአየር ክልል ላይ ሲጓዙ የነበሩት የኢትዮጵያ እና የኳታር አየር መንገድ አውሮፕላኖች የሞቃዲሾ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በሰጧቸው የተሳሳተ መረጃ ሊጋጩ ተቃርበው ነበር መባሉን ስህተት ነው ሲል የሶማሊያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን አስተባበለ።
በአንድ ሳምንት ውስጥ ሦስተኛው የምክር ቤት አባል ያለመከሰስ መብት ተነሳ
በአማራ ክልል ከተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ ለወራት በቁጥጥር ስር የሚገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል የሆኑት ካሣ ተሻገር (ዶ/ር) ያለመከሰስ መብት ተነሳ። ባለፉት ቀናት ከካሳ (ዶ/ር) በተጨማሪ የኦሮሚያ ምክር ቤት የአቶ ታዬ ደንደአን እንዲሁም የአማራ ምክር ቤት የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት አንስተዋል።
ከደብረ ብርሃን ወደ ደሴ የሚወስደው ዋና መንገድ ላልተወሰነ ጊዜ መዘጋቱ ተገለጸ
ከደብረ ብርሃን ወደ ደሴ የሚወስደው መንገድ ከዛሬ ቅዳሜ፣የካቲት 16/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ መዘጋቱ ተገለጸ።ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ በተደረገው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የማቋረጥ እርምጃ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምሥራቅ 130 ኪሎ ሜትር ከምትርቀው የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዋና ከተማ ከሆነችው ከደብረ ብርሃን የሚጀመር ነው።
በዝቋላ ገዳም 4 መነኮሳት በታጣቂዎች እንደተገደሉባት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስታወቀች
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኘው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አራት መነኮሳት የካቲት 14/ 2016 ዓ.ም. በታጣቂዎች እንደተገደሉባት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስታወቀች።
“የልጆቼን ሳቅ መስማት ለእኔ ስቃይ ነው”
የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የጤና አገልግሎት (ኤንኤችኤስ) ድረ ገጹ ላይ ባሰፈረው መረጃ አንድ ሰው በየቀኑ የሚሰማቸው ድምጾች በትክክል ከሆኑት በላይ ከፍ ብለው ከተሰሙት ሃይፐራኪዩሲስ ሊኖርበት ይችላል። ድምጹ ከፍ ብሎ ከመሰማቱ ባሻገርም አንዳንዴ ህመም ሊያስከትል ይችላል።
ህወሓት ‘እጅ በመስጠት ምሥጢር አውጥተዋል’ ያላቸውን ኬሪያ ኢብራሂምን እና ሙሉ ገብረእግዚአብሔርን አባረረ
የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ በጦርነቱ ወቅት ለፌደራል መንግሥቱ እጅ ሰጥተው ምሥጢር አሳልፈው ሰጥተዋል ያላቸውን ሁለት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱን ከፓርቲው ማባረሩን አስታወቀ።
በደብረ ብርሃን ከተማ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ኦሮሚያ ክልል መመለስ ጀመሩ
ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ከነበሩ ሰዎች መካከል የተወሰኑት ወደ ምሥራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች መመለስ ጀመሩ። ሰኞ የካቲት 11/2016 ዓ.ም. ኦሮሚያ ክልል የደረሱት የመጀመሪያ ዙር ተመላሾች፣ የቀድሞ መኖሪያቸው በሚገኙባቸው ወረዳዎች ውስጥ በተዘጋጁላቸው ጊዜያዊ መጠለያዎች ውስጥ ማረፋቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል።
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ በደረሰ የድሮን ጥቃት 30 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች ተናገሩ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃ እና ወደራ ወረዳ ሰኞ የካቲት 11/2016 ዓ.ም በአንድ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።
የአማራ እና የትግራይ ክልሎች በሚወዛገቡባቸው የራያ ወረዳዎች እየተከሰተ ያለው ምንድን ነው?
በራያ ወረዳዎች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተፈጠረው ውጥረት ቀጥሎ በዛታ ወረዳ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑን የአካባቢው ባለሥልጣናት ለቢቢሲ ገለጹ። ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ዕለት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ተሽከርካሪ ከኮረም ከተማ አንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በታጣቂዎች ጥቃት እንደተፈጸመበት ማኅበሩ ለቢቢሲ አስታውቋል።
“በሕይወት ይወጣ እንደሁ ብለን ጋራ ጋራውን እያየን ሁለት ሳምንት ሆነ” በማዕድን ዋሻ ውስጥ የተቀበረ ወጣት ወንድም
በደቡብ ወሎ ዞን፣ ደላንታ ወረዳ የከበረ ማዕድን ለማውጣት በቁፋሮ ላይ የነበሩ ማዕድን አውጪዎች በዋሻው ውስጥ ከተቀበሩ ዛሬ ሐሙስ የካቲት 14/2016 ዓ.ም. ሁለት ሳምንት ሞላቸው። በናዳ ተቀብረው የሚገኙ ሰዎች ቤተሰቦች በእነዚህ ቀናት ውስጥ ቀስ በቀስ ተስፋቸው እየተሟጠጠ በሕይወት የመውጣታቸው ነገር በእጅጉ አሳስቧቸዋል።
የአሜሪካው የንግድ ኩባንያ ጨረቃ ላይ በማረፍ ታሪክ ሠራ
አንድ የአሜሪካ ኩባንያ ጨረቃ ላይ መንኮራኩር በማሳረፍ የመጀመሪያው የንግድ ኩባንያ በመሆን ታሪክ ሠራ።
ከየፈርጁ
መሬት ላራሹ፡ የገጠሪቱን ኢትዮጵያ መልክ የቀየረው የተማሪዎች ንቅናቄ
የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ከ1950ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ዕጣ ፈንታ ላይ ወሳኝ ሊባል የሚችል ጫና አሳድሯል። ተማሪዎቹ ያነሷቸው ሁለት መሠረታዊ ጥያቄዎች የመሬት ሥሪቱ እና የብሔር እኩልነት የሚሉ ነበሩ። በየካቲት 1966 ዓ.ም ደግሞ "መሬት ላራሹ" በማለት ተማሪዎች እና ምሁራን ጥያቄውን አደባባይ አወጡት። የመሬት ስሪት ተመራማሪው አቶ ደሳለኝ ራህመቶ ደርግ ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከል ውጤታው በመሬት ባለቤትነት ላይ የተመሠረተው ሥልጣን እና ኃይልን መደምሰሱ ነው ይላሉ።
ቱርክ እና ሶማሊያ የተፈራረሙት ወታደራዊ ስምምነት ዋነኛ ትኩረቱ ምንድን ነው?
ሶማሊያ ፓርላማ ከሳምንት በፊት ከቱርክ ጋር የተፈረመውን የመከላከያ እና የምጣኔ ሃብ ስምምነትን አጽድቋል። የዚህ ስምምነት ሙሉው ዝርዝር ይፋ ባይደረግም በተለይ በመከላከያ ዘርፍ ቱርክ የሶማሊያን ባሕር ኃይልን ለማጠናከር እና የአገሪቱን የባሕር ጠረፍ በጋራ ለመጠበቅ ከስምምነት መደረሱ ተነግሯል።
በስዊዲን የደኅንነት መሥሪያ ቤት ውስጥ በተፈጠረ ያልታወቀ ሽታ 8 ሰዎች ሆስፒታል ገቡ
በስዊዲን የደኅንነት መሥሪያ ቤት ውስጥ ባጋጠመ ያልተለመደ ዓይነት ሽታ ምክንያት ስምንት ሰዎች ሆስፒታል ሲገቡ ሠራተኞቹ ሕንጻውን ለቀው እንዲወጡ መደረጉ ተነገረ።
ሳይተዋወቁ አንዳቸው የሌላኛውን ሕይወት የታደጉት ሁለት ግለሰቦች
ሁለት የማይተዋወቁ ሰዎች አንዳቸው የሌላኛውን ሕይወት ታድገዋል። በዜግነት የማይገናኙት ሁለቱ ሰዎች አንደኛው የዩናይትድ ኪንግደም ዜጋ ሲሆን፣ ሌላኛው ጀርመናዊ ነው። እንዴት? ታሪኩ እንዲህ ነው።
ታዋቂ ሰዎች የህጻናት የዱቄት ወተትን ማስተዋወቃቸው ለምን አሳሳቢ ሆነ?
የዓለም ጤና ድርጅት ሕፃናት ስድስት ወር እስኪሞላቸው ድረስ የእናታቸውን ጡት ወተት እየጠቡ እንዲያድጉ፤ መንግሥታትም ይህ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ይመክራል። አሁን ደግሞ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚቀርቡ የዱቄት ወተት ማስታቂያዎችን ለማስቆም ዘመቻ ከፍቷል።
ለበርካቶች የሙዚቃ ጉዞ መነሻ የሆነችው ዊትኒ ሂዩስተን እና ዘመን ተሻጋሪ የሙዚቃ ሥራዋ
ከ12 ዓመታት በፊት በየካቲት 2012 እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ያረፈችው ዊትኒ ሂዩስተን፣ የበርካታ ትውልዶችን ሕይወት በሙዚቃ ሥራዎቿ ነክታለች። ሥራዎቿ አሁንም በመላው ዓለም በሚገኙ ሚሊዮኖች እየተደመጡ ይደነቃሉ፤ በርካቶች ደግሞ ከሙዚቃ ብቃቷን ለመማር ድምጻቸውን በእርሷ ሥራዎች ይሞርዳሉ። ዊትኒ ብቃቷን ለዓለም ያሳየችው በሙዚቃ ሥራዎቿ ብቻ ሳይሆን በፊልሙም በኩል የተዋጣላት ተዋናይት እንደሆነች አስመስክራለች።
ፈረንሳይ ስለምታስተናገደው የዘንድሮው የፓሪስ ኦሊምፒክ የምናውቃቸው ዋና ዋና ጉዳዮች
በአውሮፓውያኑ በጋ የሚካሄደው የፓሪስ ኦሊምፒክስ ከሐምሌ 19 እስከ ነሐሤ 5 ባለው ጊዜ ይከናወናል። 10500 አትሌቶች በሚሳተፉበት ውድድር 32 ጨዋታዎች የተካተቱ ሲሆን 329 ሜዳሊያዎች ለሽልማት ተዘጋጅተዋል።
በአዲስ አበባ ባለፉት 6 ወራት 15 የእሳት ቃጠሎዎች ሆነ ተብሎ መፈጸማቸው ተነገረ
በስድስት ወራት ከደረሱት የእሳት ቃጠሎዎች 16 ያህሉ ሆን ተብለው የተፈጸሙ መሆናቸውን እና ከእነዚህም መካከል 15ቱ በአዲስ አበባ መከሰታቸውን የፌደራል ፖሊስ በፎረንሲክ ምርመራ ማረጋገጡን አስታወቀ።
ኬንያ ከአዲሱ አሠራሯ ውጪ ኢትዮጵያውያን ያለክፍያ ወደ አገሯ እንዲገቡ ፈቀደች
ኬንያ ወደ ግዛቷ ለሚገቡ አፍሪካውያን ቪዛ መጠየቋን ካቆመች በኋላ ከጀመረችው አዲስ የጉዞ ፈቃድ ማረጋገጫ ጥያቄ እና ክፍያ ኢትዮጵያውያን ነጻ እንዲሆኑ መወሰኗን በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አስታወቁ።
መንግሥት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ሰላማዊ ተቃውሞ ለማፈን እየተጠቀመበት ነው ሲል አምነስቲ ከሰሰ
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት “ሰላማዊ የተቃውሞን” ለማፈን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እየተጠቀሙበት ነው ሲል ዓለም አቀፉ የመብቶች ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ።
የአፍሪካ ኅብረት የአህያ ቆዳ ንግድን በመላው አህጉሪቱ እንዳይካሄድ አገደ
የአፍሪካ ኅብረት አዲስ አባባ ላይ ያካሄደውን የመሪዎች ጉባዔን ተከትሎ በመላው አፍሪካ አወዛጋቢ የሆነው የአህዮች ቆዳ ንግድ እንዳይካሄድ እገዳ ጣለ።
አጃኢብ!
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪና ማሽከርከር ምን ያህል ያዋጣል?
ዓለም በተሽከርካሪዎች በኩል ከነዳጅ መኪኖች በኤሌክትሪክ ወደ ሚንቀሳቀሱት ፊቱን እያዞረ ነው። ኢትዮጵያም ይህንን አቅጣጫ የተከተለ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው። ቢሆንም ግን ከኤሌክትሪክ መኪኖች ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጉዳዮች ይነሳሉ። እነዚህን መኪኖች መኪኖች ማሽከርከር ምን ያህል አዋጪ ነው?
“በሕይወት ለመቆየት የዱር ፍሬ እየበላን ነው”
በትግራይ የተካሄደውን ጦርነት ተከትሎ በተከሰተው የምግብ እጥረት ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ መጋለጣቸውን የክልሉ ባለሥልጣናት ከመግለጻቸው በተጨማሪ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች እንደሞቱ ይናገራሉ። በዚህም ሳቢያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታዳጊዎች ለእራሳቸው እና ለቤተሰባቸው ምግብ የሚሆን የዱር ፍሬ ለማግኘት ከትምህርት ቤት ይቀራሉ ወይም ትምህርት ያቋርጣሉ።
በዓለም ዙሪያ እየተስፋፋ ስለመጣው የሳንባ ምች በሽታ መታወቅ ያለባቸው 5 ነጥቦች
ከኮቪድ መከሰት በኋላ በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ አገራት ጉንፋን መሰል የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች በተደጋጋሚ እየታዩ ናቸው። በዚህም ሳቢያ እንደ ሳንባ ምች ያሉ በሽታዎች ክስተት መጠን ባልተለመደ መልኩ በዓለም ዙሪያ መጨመራቸው ሪፖርት ተደርጓል። ከእነዚህም መካከል ስለሳንባ ምች ልናውቃቸው የሚገቡ ጠቃሚ ነጥቦችን እነሆ. . .
ስለልጆች አስተዳደግ በዩቲዩብ በመምከር ታዋቂ የሆነችው አሜሪካዊት ልጇቿን በማሰቃየት ተፈረደባት
ወላጆች ልጆቻቸው ሥርዓት ለማስተማር አስከፊ አያያዝን እንዲከተሉ በዩቲዩብ በመምከር ታዋቂ ለመሆን የበቃችው አሜሪካዊቷ የዩታህ ግዛት እናት ልጆቿን በማሰቃየት ተከሳ የዓመታት እስር ተፈረደባት።
ለቀናት ብቻ በሕይወት ይቆያሉ የተባሉት ተጣብቀው የተወለዱት መንትዮች 7 ዓመት ሆናቸው
ተጣብቀው የተወለዱት ማሪየሜ እና ንዲዬ ከተወለዱ በኋላ ከጥቂት ቀናት በላይ በሕይወት አይቆዩም ተብሎ ነበር። አሁን ግን ሰባት ዓመት ሆኗቸዋል፤ በአውሮፓ ውስጥም ተጣብቀው ተወልደው ይህን ያህል ዓመት ቆዩ የመጀመሪያዎቹ መንትዮች ናቸው ተብሎ ይታሰባል።
‘ንቦችን ለማገዝ’ የማር እንጀራን በ3ዲ የሚያትመው ኢትዮጵያዊ ወጣት
በዓለም ላይ ተፈላጊ ከሆኑ ለምግብ እና ለሌሎች አገለግሎት የሚውለውን ማር የሚያመርቱት ታታሪዎቹ ንቦች ማር ከሚሠሩበት ጊዜ በላይ የማር እንጀራን ለማዘጋጀት ረዘም ያለ ጊዜ ይፈጅባቸዋል። ይህም በማር ምርታቸው ላይ ተጽእኖ አለው። ናትናኤል ታዲያ ንቦቹን ለማገዝ አዲስ ፈጠራን አዘጋጅቷል።
ስለ ሬጌው ንጉሥ ቦብ ማርሌይ አራት አስገራሚ እውነታዎች
ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ ከፍተኛ ፍቅር የነበረው የራስ ተፈሪያን እምነት ተከታዩ ቦብ ማርሌይ ምንም እንኳን ስሙ ከዓለም ጫፍ እስከ ጫፍ ቢናኝም ስለእሱ አንዳንድ አስገራሚ እውነታዎች ይሰማሉ። ስለ ሬጌው ንጉሥ ብዙም የማይታወቁ አራት ነገሮችን እነሆ. . .
ወደፊት ሊከሰት የሚችለው ‘ወረርሽኝ ኤክስ’ ምንድን ነው? ከኮቪድ የበለጠ ሕዝብ ሊጨርስ ይችላል?
የዓለም የምጣኔ ሃብት ጉባኤ በዳቮስ፣ ስዊትዘርላንድ ባለፈው ሳምንት ተካሂዷል። ጎን ለጎን የዓለም ጤና የሚያሳስባቸው ትልልቅ መሪዎች በር ዘግተው ለቀናት መክረዋል። እንደ ኮቪድ ያለ አዲስ ወረርሽኝ ከመምጣቱ በፊት ምን ይደረግ? እንዴት እንዘጋጅ በሚለው አጀንዳ ነው የተወያዩት። ለጊዜው መጪውን ወረርሽኝ ስሙን “በሽታ ኤክስ” በሚል ይዘውታል።
ዶናልድ ትራምፕ በስማቸው የሚጠራውን አዲስ የስኒከር ጫማ ምርትን አስተዋወቁ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በራሳቸው ድርጅት የተመረተ እና በስማቸው የሚጠራ የስኒከር ጫማ ምርትን ይፋ በማድረግ ለገበያ አስተዋወቁ።
ፑቲን ለሰሜን ኮሪያው መሪ ቅንጡ መኪና መስጠታቸው ከደቡብ ኮሪያ ተቃውሞ ገጠመው
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በአገራቸው የተሠራ ቅንጡ መኪና በስጦታ ማበርከታቸውን ደቡብ ኮሪያ ተቃወመች።
የሦስት ዓመትን ሕጻን ከእንግሊዝ ወደ ኬንያ በመውሰድ ያስገረዘችው ሴት እስር ተፈረደባት
የሦስት ዓመት እንግሊዛዊት ሕጻንን ወደ ኬንያ በመውሰድ ያስገረዘችው ሴት እስር ተፈረደባት።በሰሜን ምሥራቅ ለንደን፣ ሃሮው ነዋሪ የሆነችው የ40 ዓመቷ አሚና ኑር ሕጻኗን ለማስገረዝ ወደ ኬንያ የወሰደቻት እንደ አውሮፓውያኑ በ2006 ነበር። ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የወንጀለኞች ፍርድ ቤቱ ኦልድ ቤሊይ ዓርብ ዕለት በዋለው ችሎት ኑር በዚህ ድርጊቷ ሰባት ዓመታትን በእስር እንድታሳልፍ ብይን ሰጥቷል።
የምጽአት ቀን መቃረብን ስለሚቆጥረው ሰዓት ሰምተዋል? እውን የዓለምን ፍጻሜ የሚያመለክት ነው?
የምጽአት ቀን ሰዓትን የሚቆጥሩ ሳይንቲስቶች በየዓመቱ ምን ያህል ወደ ዓለም ፍጻሜ እየቀረብን እንደሆነ የሚያሳይ ሥዕል ያወጣሉ። እነሆ በ2024 ለ76ኛ ጊዜ ይህን አድርገዋል። በተጨማሪም በየዓመቱ አንድ ወደ መዳረሽን የሚያቀርበን ምክንያት ይመርቁበታል። እውን ይህ ሰዓት የዓለም ፍጻሜን አመላካች ነው?
የተመለሱ ጥያቄዎች
የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል-ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ምንድነው? አባላቱስ እነማን ናቸው?
ግዴታቸውን የማይወጡ የኔቶ አባል አገራት ላይ ሩሲያ የፈለገችውን ብታደርግ ግድ እንደማይሰጣቸው እንዲያውም ጥቃት እንዲፈጸምባቸው እንደሚያበረታቱ ትራምፕ ሰሞኑን መናገራቸው ቁጣን ቀስቅሷል። ሰባ አምስት ዓመታትን ያስቆጠረው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል-ኪዳን ድርጅት ኔቶ ዓላማው ምንድን ነው? አባላቱስ እነማን ናቸው?
በሴቶች ላይ ሊከሰት የሚችለውን ካንሰር ስለሚከላከለው ክትባት ምን ያውቃሉ?
አንድጥናት የኤችፒቪ ክትባት በማህፀን በር ጫፍ ካንሰር የመያዝ ዕድልን በ90 በመቶ እንደሚቀንስ አመልክቷል። በመላው ዓለም በርካታ ሴቶች በብዛኛው ከሚያዙበት የካንሰር ዓይነቶች መካከል የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
የወንጀል ተጠርጣሪዎች መታሰር ያለባቸው የት ነው? በምን ሁኔታስ ሊያዙ ይገባል?
በኢትዮጵያ የሚከሰቱ ተቃውሞዎች እና አለመረጋጋትን ተከትሎ በርካቶች በጅምላ ስለሚታሰሩባቸው የአዋሽ አርባ እና የአዋሽ ሰባት ወታደራዊ ካምፖች ታሪክ እና በእነዚህ ስፍራዎች የታሰሩ ሰዎችን ታሪክ በሦስት ክፍል አቅርበናል። እነሆ ለማጠቃለያ ተጠርጣሪዎች የት እና በምን ሁኔታ ሊያዙ እንደሚገባ ከሕግ እና ከመብት ጥበቃ አንጻር ቃኝተናል።
በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማፂያን ለምን ከአሜሪካ እና አጋሮቿ ጋር ጦርነት ውስጥ መግባትን መረጡ?
ነገር ግን ይህ ጦርነት በቀላሉ የሚወጡት እንዳልሆነ እሙን ነው። አራን በገንዘብ የምትደግፋቸው የሁቲ አማፂያን ካለፈው ኀዳር ወር ጀምሮ ቀይ ባሕርን አቋርጠው በሚጓዙ የንግድ መርከቦች ላይ ከ30 በላይ ጥቃቶች ሰንዝረዋል። የዩኤስ መከላከያ ባለሥልጣናት አማፂያኑን ሳንደመስስ አርፈን አንቀመጠም እያሉ ነው።
ልጆች በሚጠቀሟቸው የቆዳ ቅባቶች ይዘት ላይ ወላጆች ቁጥጥር እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ
በመላው ዓለም ታዳጊዎች የውበት መጠበቂያ ምርቶች የመጠቀም ልማድ መስፋፋት ልጆችን ሊድን ለማይችል የቆዳ በሽታ ሊያጋልጣቸው እንደሚችል የብሪታኒያ የቆዳ ሐኪሞች ማኅበር አስጠነቀቀ።
ቪዲዮ, ለጨቅላ ሕጻናት የሚሠጠው በዓለም የመጀመሪያው የወባ መከላከያ ክትባትርዝመት, 1,53
በመላው ዓለም የወባ በሽታ በዓመት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት ይዳርጋል። የዓለም ጤና ድርጅት ማረጋገጫ የሰጠውን ክትባት ጨቅላ ሕጻናትን በመከተብ ካሜሩን የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች። ካሜሩን በአውሮፓውያኑ 2024 እና 2025 ለ250 ሺህ ሕጻናት ክትባቱን ለመስጠት አቅዳለች። ነገር ግን በአገሪቱ ለክትባት ከሚሰጠው ግምት አንጻር ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍል ማሳመን ፈተና ሊሆን ይችላል።
በመላው ዓለም አሳሳቢ እየሆነ ስለመጣው ኩፍኝ ሊያውቋቸው የሚገቡ ነጥቦች
የዓለም ጤና ድርጅት እና የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) እአአ ከ2023 መጨረሻ ጀምሮ የኩፍኝ በሽታ በልጆች ላይ የደቀነው ስጋት ቀጥሏል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ለልጆቻችን እና ለራሳችን ጤና ስለብሽታው ሊያውቋቸው የሚገቡ ነጥቦችን እዚህ ያንብቡ።
ለእንቅልፍ የሚውለውን ሜላቶኒን ከመጠን በላይ ሲወስዱ ምን ይገጥመዎታል?
ሜላቶኒን እንቅልፍ በሚያስቸግራቸው ሰዎች ተወዳጅነትን እያተረፈ ያለ አጋዥ ንጥረ ነገር ነው። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሜላቶኒንን ከመጠን በላይ መውሰድ በጣም እየጨመረ ይገኛል። ንጥረ ነገሩን ከመጠን በላይ መውሰድ ምን ያህል ጉዳት ያደርሳል?
ከወጪ ጋር በተያያዘ ፕሪሚየር ሊጉ ለምን ክለቦችን ይቀጣል?
ኤቨርተን እና ኖቲንግሃም ፎረስት የፕሪሚር ሊጉን የፋይናንስ ሕጎች ጥሰዋል በሚል አዲስ ክስ ተመስርቶባቸዋል። ኤቨርተን ከዚህ ቀደም በቀረበበት ክስ 10 ነጥብ ተቀንሶበት ይግባኝ ጠይቋል። ቢቢሲ በጉዳዩ ዙሪያ ሚነሱ ጥያቄዎችን እንደሚከተለው ተመልክቷቸዋል።
የማኅጸን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት ለማን ይሰጣል? በኢትዮጵያስ ማግኘት ይቻላል?
የማኅጸን በር ጫፍ ካንሰር በዓለም ላይ አራተኛው ገዳይ የካንሰር ዓይነት ነው። በየዓመቱ 300 ሺህ ሰዎችን ይገድላል። ጥናቶች የበሽታው መከላከያ ክትባት 90 ከመቶ የማኅጸን በር ጫፍ ካንሰርን እንደሚከላከል ያሳያሉ።
ተመራማሪዎች ከሰው ዐይነ ምድር የአውሮፕላን ነዳጅ ፈጠሩ
የሰው ልጆች ዐይነ ምድር የአውሮፕላን ነዳጅን ለመተካት የተሻለ አማራጭ ሆኖ ቀርቧል። በዚህ ሂደት ውስጥ መጀመርያ ልክ እንደ ነዳጅ ሁሉ ድፍድፍ የሆነ ነገር ይፈጠራል፣ ከዚያ ወፍራም ጥቁር ፈሳሽ ሆኖ ከኬሚካሎች ጋ ተቀላቅሎ ነው ወደ ነዳጅነት የሚቀየረው። ይህ ግኝት ገና በላቦራቶሪ ደረጃ ያለ ሲሆን ወደ ተግባር ለመሄድ በጣም ረዥም ዓመታት ሊወስድ ይችላል። እያንዳንዱ የሰው ልጅ በዓመት በአማካይ 5 ሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ መሥሪያ የሚሆን ዐይነ ምድር ያስወግዳል።